የወገን ጥምር ጦር የፀረ ማጥቃት ርምጃ፣ ወራሪውን መንጋ መውጫ መግቢያ እያሳጣው ነው! - ኢዜአ አማርኛ
የወገን ጥምር ጦር የፀረ ማጥቃት ርምጃ፣ ወራሪውን መንጋ መውጫ መግቢያ እያሳጣው ነው!
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የአማራ ልዩ ኃይል ፋኖና ሚሊሺያ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት ርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ ነው።
ጠላት በእነዚህ አካባቢዎች ያሰለፈው ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
ከጥቃቱ የተረፈውም እግሬ አውጪኝ በማለት እየፈረጠጠ ይገኛል።
ጠላት ያሰለፈው መንጋ ይዞት የመጣው መሣሪያ ገሚሱ ከጥቅም ውጭ ሲደረግ ገሚሱ ተማርኳል።
የጸጥታ ኃይላችን በወራሪው የሽብር መንጋ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ኪሳራ በመሸሽ በየሸጡ፣ በየወንዙና በየጋራው እየተሽሎከሎከ የሚገኘውን የተበታተነ የጁንታ መንጋ፣ የየአካባቢው ሚሊሺያና አርሶ አደር ተደራጅቶ በመከታተል፣ የሀገር ደጀንነቱን ሊያጠናክር ይገባል።
እስካሁንም ከጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን የቆመው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሺያ ከየአካባቢዎቹ ነዋሪ ጋር እየፈጸመው የሚገኘው አኩሪ የጦር ሜዳ ገድል ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት