ቀጥታ፡

አሸባሪውን ህወሓት እየደመሰሰ ለሚገኘው ሠራዊት ደጀንነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 15/2014(ኢዜአ) አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እየደመሰሰ ለሚገኘው ሠራዊት ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በደሴ ከተማ የሚገኙ የመረዳጃ ዕድሮች አስታወቁ።

የመረዳጃ ዕድሮቹ አባላት በወሎ ግንባር አሸባሪውን የህወሓት ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ እየተፋለመ ለሚገኘው ሠራዊት በግንባር ተገኝተው የምሳ ግብዣ አድርገዋል።

የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ አቶ ዘርይሁን ማንደፍሮ ወራሪውን ኃይል እየደመሰሰ ለሚገኘው ጀግና ሠራዊት ደጀንነታቸውን ለማሳየት በግንባር መገኘታቸውን ገልጸዋል።

የአሸባሪው ኃይል ግብዓተ መሬት እስከሚፈጸም ድረስ የደጀንነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

መሰል አደረጃጀቶች የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን የህወሓት ወራሪ ኃይል ለማጥፋት ተጋድሎ እያደረገ ለሚገኘው ሠራዊት ደጀንነታቸውን በተግባር እንዲያስቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም