የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ አሳሳቢ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ አሳሳቢ ነው
ጥቅምት 15 / 2014 (ኢዜአ) የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡
የኢጋድ ስራ አስፈጻሚ በወቅታዊ የሱዳን ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡
የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው፤ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢጋድ ሥራ አስፈፃሚ የሱዳን ሽግግር መንግሥትን ለማዳከም የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ አጥብቆ የሚያወግዝ መሆኑንም ገልጿል።
ኢጋድ የሱዳንን የሽግግር መንግስት ለመደገፍ፣ የህዝብ ሰላምን እና ዴሞክራሲን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ሱዳን የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር እና መስራች አባል ነች።
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የአውሮፓ ኅብረትና ሌሎች ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሁኔታው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።