ቀጥታ፡

ወጣቱ የአይቲ ባለሙያ የግንባታ ስራ መቆጣጠርያ ሶፍትዌር ፈጠረ

ጅማ ጥቅምት 10/2014 (ኢዜአ) ወጣቱ የአይቲ ባለሙያ የግንባታ ስራዎችን ለመቆጣጠርና ለመከታተል የሚያስችል ሶፍትዌር ፈጠረ።

በጅማ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ታምራት ታንጋ የፈጠረው ሶፍትዌር "አውቶሜትድ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት  ኢንፎርሜሽን ሲስተም" የተሰኘ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ነው።

የፈጠራው ባለቤት ወጣት ታምራት ታንጋ  ለኢዜአ እንዳለው የኮምፒዩተር ሶፍትዌሩ የግንባታ ስራን በመከታተልና በመቆጣጠር የግንባታው ሂደት የደረሰበትን ደረጃና የክፍያ ሁኔታን የሚያመላክት ነው።

ሶፍት ዌሩ "ሙሉ የግንባታ ወረጃዎቹ ማለትም ግንባታው መቼ ተጀመረ፣ ስንት ጊዜ ሆነው፣ ያለበት ደረጃና የክፍያ ሁኔታ ምን ይመስላል? የመሳሰሉትን መረጃዎችን በተተነተነ መልኩ ማቅረብ የሚያስችል ነው" ብሏል።

እንደ ሶፍትዌር ዲዛይነሩ ገለጻ የበላይ አካላትና የሚመለከታቸው ዘርፎች የዘገዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ለምን አንደዘገዩ ለመለየትና የግንባታ ደረጃውና የክፍያ ሁኔታው ካልተመጣጠነ መጠየቅ እንዲችሉ ያግዛል"።

ሶፍተ ዌሩ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በእንግሊዝኛ የሚሰራ ሲሆን የግንባታ ተቋማት በዌብ ሊንኩ አማካኝነት የሚጠቀሙበት እንደሆነም ተናግሯል።

"ሶፍት ዌሩ ስለ ግንባታ ስራው የንዑስ ስራ የጨረታ አወጣጥ ሀኔታ፣ የተፈጠረ የስራ እድል፣ ያጋጠመ ችግር፣ በተመለከተም የተሟላ የበይነ በረብ ሪፖርት ይሰጣል" ብሏል።

የጅማ ዞን  የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ናስር ሙሳ በበኩላቸው "ሶፍትዌሩ በየጊዜው የሚገባለትን መረጃ በማቀናጀትና በመተንተን የተጣራ መረጃን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል" ብለዋል።

በዘርፉ ያሉ ችግሮችን እንደሚያስቀር ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም ሶፍት ዌሩ ለመቆጣጠር የተፈለገው የቦታ ክልል ውስጥ ያለን ማንኛውም የግንባታ ስራ ጊዜና ጉልበት ሳያባክን በቀላሉ መከታተል ያስችላል" ብለዋል።

በተጨማሪም ሶፍት ዌሩ ድርጅቶች፣ ማህበራትና ግለሰቦች  የሚያወጡትን  የተለያዩ የግንባታ የሞያ ፍቃድ በመለየት የሚያሳውቅና የሚያጋልጥ በመሆኑ ወጥ አሰራር እንዲሰፍን የሚያግዝ እንደሆነም ተናግረዋል።

ወጣት ታምራት ታንጋ ለሰራው የሶፍትዌር ፕሮግራም የኢትዮጵያ እምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት የፈጠራ ባለቤትነት መብት የምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም