ቀጥታ፡

አሸባሪውን ህወሃት በተባበረ ከንድ እስከወዲያኛው ማጥፋት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14/2014(ኢዜአ)  አሸባሪውን ህወሃት በተባበረ ክንድ እስከወዲያኛው ማጥፋት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅንቄ /አብን/ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ተናገሩ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅንቄ /አብን/ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም ጨምሮ የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር አባላት በደሴና አካባቢዋ ያለውን የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

ወራሪውና አሸባሪው ህወሃት ህዝብን ለማሸበር "ኮምቦልቻ፤ ደሴና አካባቢዋን ተቆጣጥሪያለሁ" ብሎ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ የወያኔን የውሸት ወሬዎች በአግባቡ በመረዳት "ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ወሎ የወራሪው ኃይል መቀበሪያ እንዲሆን መስራት አለባቸው" ብለዋል።

አሸባሪው ቡድን በርካታ ጀሌና ተዋጊ ኃይል በአፋርና አማራ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በማሰማራት ወረራ ማካሄዱን ጠቅሰው፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና በአርሶ አደሮች ጭምር እየተመታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

"በተካነበት ፕሮፖጋንዳ ደሴ፣ ሃይቅ እና ኮምቦልቻን ተቆጣጥሪያለሁ" በማለት የሚነዛው ወሬ ህዝብን ለማሸበር መሆኑንም አቶ የሱፍ ገልጸዋል።

የወራሪውን ኃይል የኢትዮጵያ ልጆች በጋራ ሆነው እየመቱት መሆኑን ገልጸው፤ አሁን ላይ ያለውን ሃይል በሙሉ አሟጦ እየተጠቀመ ቢሆንም "በወሎ ግንባር ግብአተ መሬቱ ይጠናቀቃል" ብለዋል።

በመሆኑም በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘውን አሸባሪው ህወሃትን በተባበረ ክንድ እስከወዲያኛው ማጥፋት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም በመልት ገልጸዋል።

አብን የአደረጃጀት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በበኩላቸው፤ አሸባሪ ህወሃት በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለማጠናቀቅ የአገር መከላከያ ሰራዊት የአማራና ሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች፣ ፋኖ እና ሚኒሻው "በትብብር መዘጋጀታቸውን ተመልክተናል" ብለዋል።

"በሽብር ቡድኑ የውሸት ወሬዎች እና ውዥንብር ማህበረሰቡ ቤትና ንብረቱን ትቶ እንዳይሰደድ" ሲሉ መልእክታቸውን አስተላለፍዋል።

የደሴ ከተማና አካባቢዋ ማህበረሰብ በሽብር ቡድኑ ፕሮፓጋንዳ ሳይደናገር የእለት እንቅስቃሴውን በማከናወን ላይ መሆኑን የኢዜአ ሪፖርተር በስፍራው ተገኝቶ ተመለክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም