ቻይና ለኢትዮጵያ 800 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደረገች

65

ጥቅምት 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) ቻይና ለኢትዮጵያ ሲኖፋርም የተባለው 800 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አደረገች።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛዎ ዚዮሃን ለጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አስረክበዋል፡፡

ቻይና እ.ኤ.አ ከመስከረም 2020 ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተለያዩ አገሮች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ ማድረጓ ይታወሳል።

የቻይና መንግስት ከሁለት ቢሊዮን ዶዝ በላይ ክትባት በመላው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ 100 ሚሊዮኑ በማደግ ላይ ላሉ አገሮች የሚከፋፈል መሆኑ ታውቋል።ቻይና እስካሁን ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት መለገሷን ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም