'አንጎድልም' የተሰኘ የግጥም መድብል በብሔራዊ ቴአትር ቤት እየተመረቀ ነው

ጥቅምት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) በመከላከያ ሰራዊት አባላት የተደረሰ 'አንጎድልም' የተሰኘ የግጥም መድብል በብሔራዊ ቴአትር ቤት እየተመረቀ ነው።

79 ግጥሞችን ያሰባሰበው 'አንጎድልም' የግጥም መፅሐፍ በ96 ገፆች ተቀኖብቦ የቀረበ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከገጣሚዎቹ አንዱ የሆኑት ኮሎኔል ተስፋዬ ኤፍሬም ጥበብና ወታደሩ ያላቸውን ትስስር አብራርተዋል።

መጽሐፉ 100 ብር የመሸጫ ዋጋ የወጣለት ሲሆን የገቢው 30 በመቶ ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት ጦርነት ተጎጂ ለሆኑ ቤተሰቦች ድጋፍ ይውላል ተብሏል።

በፕሮግራሙ ላይ ብርጋዴል ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የመከላከያ መኮንኖች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም