በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ190ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ190ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ
ጥቅምት 11/2014 (ኢዜአ) በአሜሪካን ሀገር ዴንቨር፤ አውሮራና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሽብርተኛው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ190 ሺ በላይ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።
ዴንቨር፤አውሮራና የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቤይ ኤርያ ቀጥሎ 2ኛውን ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።
አምባሳደሩ እንደገለጹት ኢትዮጵያውያኑ በሽብርተኛው ህወሃት በግፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ190 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
በአሜሪካ ከወገን ለወገን የሚደረገው ድጋፍ እየጨመረ መሆኑንና በሌሎች ቦታዎችም ድጋፍ ለማካሄድ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
ዝግጅቱ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት፣ ለአርቲስት ተስፋዬ ሲማ እና ለለጋሾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።