ቀጥታ፡

አሸባሪው ህወሃት በውርጌሳ ከተማ 13 ንፁኃን ዜጎች ላይ ጋዝ በማርከፍከፍ በጭካኔ ረሽኗል

ጥቅምት 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል በውርጌሳ ከተማ 13 ንፁኃን ዜጎች ላይ ጋዝ በማርከፍከፍ በጭካኔ መረሸኑ የዐይን እማኞች ገለጹ።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወራሪ ኃይል በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በርካታ ንፁኃን ወገኖችን በግፍ እየጨፈጨፈ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በውርጌሳ ከተማ የተፈጸመው የ13 ንፁኃን ዜጎች ጭፍጨፋም የጥፋት ቡድኑ ለአካባቢው ህዝብ ያለው የመረረ ጥላቻ የቀጠለ ሰይጣናዊ ምግባር ሁነኛ ማሳያ መሆኑን የዐይን እማኞች ተናግረዋል።

እማኞቹ በማከልም ቡድኑ በአማራ ምድር ውሎ ካደረ ከዚህ የባሰ የንፁኃን ጅምላ ፍጅት ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል ገልጸዋል።

በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተለይም በጦርነት ቀጠና ያለው የህብረተሰብ ክፍል እራሱን በሚገባ አደራጅቶ ሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል መደምሰስ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ህዝብ በወራሪው የህወሃት አሸባሪ ኃይል ያጋጠመውን የህልውና አደጋ መመከት የሚቻለው አንድነትን አጠናክሮ መታገል ሲቻል እንደሆነም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም