ቀጥታ፡

በደቡብ ሱዳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ10 ሺህ ዶላር የቦንድ ግዢ ተፈጸመ

ጥቅምት 10፣2014 (ኢዜአ) በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ10 ሺህ ዶላር የቦንድ ግዢ ፈጽመዋል።

የቦንድ ግዥውን የፈጸሙት በደቡብ ሱዳን ተሠማርቶ የሚገኘው በኤርትራዊያን ባለቤትነት የሚንቀሳቀሰው ኢዝራ የልማትና ኮንስትራክሽን ግሩፕ እና ጄድኮ ኩባንያ ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውን መሃንዲሶች ናቸው።

በዚህም በኤርትራውያን ባለቤትነት የሚንቀሳቀሰው ኢዝራ የልማትና ኮንስትራክሽን ግሩፕ ለግድቡ 8 ሺህ ዶላር ቦንድ ግዥ ሲፈጽም የጄድኮ ኩባንያ መሃንዲሶች ደግሞ 2 ሺህ ዶላር ፤ በድምሩ የ10 ሺህ ዶላር ቦንድ ግዥ ተፈጽሟል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ለኢዝራ ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገብረንጉስ እዝራ እና ለጄድኮ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ ጠንክር ቦንዱን አስረክበዋል።

አምባሳደሩ ከዚህ ቀደም ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ በገቡት ቃል መሠረት የህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛታቸው ለኩባኒያዎቹ አመራሮችና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም