ቀጥታ፡

ማርክ ፎርክነር ከ737 ማክስ ደኅንነት ጋር በተያያዘ ክስ ቀረበበት

ጥቅምት 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቀድሞ የቦይንግ ኩባንያ ቴክኒክ አብራሪ ማርክ ፎርክነር የ737 ማክስ አውሮፕላን ምዘና እና ፍቃድ አሰጣጥ ላይ የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደርን አጭበርብሯል በሚል ክስ ቀረበበት።

የፍርድ ቤት ሰነዶች ማርክ ፎርክነር ለአውሮፕላኑ የበረራ መቆጣጠሪያ ስርዓት አዲስ ክፍል ሐሰተኛ፣ ትክክለኛ ያልሆነ እና ያልተሟላ መረጃ ለፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር እንደሰጠ ይናገራሉ።

አሳሳች የተባለው መረጃ በ 2018 እና በ 2019 በኢንዶኔዥያ እና በኢትዮጵያ በ737 ማክስ አደጋዎች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ ያደርገዋል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ከሁለት ዓመት በፊት የኢንዶንዢያው ላየን ኤር እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ ከደረሰው አሰቃቂ አደጋ ጋር ተያይዞ አውሮፕላኑ ከበረራ ውጪ እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም