ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሺ 526 ተማሪዎችን አስመረቀ

83

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 06 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 526 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ያስመረቃቸው ተማሪዎች በቀን፣ በማታ፣ በርቀት፣ በክረምት እና በቅዳሜ እና እሁድ ቀናት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ምሩቃኑ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በማስተርስ እና በዲፕሎማ የሰለጠኑ ሲሆን፤ 1 ሺህ 285 ወንዶች እና 1 ሺህ 241 ሴቶች ናቸው።በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የዩንቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ (የክብር ዶክተር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ሌሎች የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

ዩኒቨርሲቲው "ኮተቤ ሜትሮፓሊታን" የሚለውን ስያሜውን ወደ "ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ" መቀየሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ ተመራቂዎች ራሳቸውን በቀጣይ በእውቀት ብሎም በትምህርት ሊያጎለብቱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የእድገት እና የብልጽግና ጉዞ ለማሻገር የአሁኑ ትውልድ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በመመከት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

"ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ" ስሙ ወደ "ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ" እንዲቀየር መወሰኑ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም