የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የጋራ ትብብሮች መጠናከር አለባቸው - ኢዜአ አማርኛ
የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የጋራ ትብብሮች መጠናከር አለባቸው
ጥቅምት 5/2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ከሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ዴቪድ ፍራንሲስ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የጋራ ትብብሮች ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የጋራ ትብብሮች ማጠናከር ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ትናንት እና ዛሬ ከ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በሚያስችሉና በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይቶች አድርገዋል።