ቀጥታ፡

ቦርዱ የሐረሪ፣ የሶማሌ እና የደቡብ ክልሎች ላይ አጠቃላይ ምርጫ የተከናወባቸው ምርጫ ክልሎችን ውጤት ይፋ አደረገ

ጥቅምት 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሐረሪ፣ የሶማሌ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ላይ አጠቃላይ ምርጫ የተከናወባቸው ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ አደረገ።

ውጤቱ በተገለጸባቸው የምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች የብልጽግና ፓርቲ ያሸነፈ ሲሆን በሶማሌ ክልል አንድ የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ላይ የግል ተወዳዳሪ አሸንፈዋል።

በ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሣ ምርጫ ባልተከናወነባቸው ሌሎች ምርጫ ክልሎች ደግሞ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም የድምፅ አሰጣጥ ሂደት መከናወኑ ይታወሳል።

በሐረሪ በሁለት የምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት መቀመጫ አግኝቷል።

በሶማሌ ክልልም ካለው 23 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 23ቱንም የብልጽግና ፓርቲ አግኝቷል።

እንዲሁም በደቡብ ክልል ምርጫ በተካሄደባው 22 የምርጫ ክልሎች 19 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የብልጽግና ፓርቲ ያገኘ ሲሆን ሶስት የምርጫ ክልሎች አቤቱታ ያለባቸው በመሆኑ ውጤቱ በዛሬው ዕለት ሳይገለጽ መቅረቱን የቦርዱ መረጃ አመልክቷል።

በክልል ምክር ቤት ደግሞ በደቡብ ክልል በተመሳሳይ ሶስት የምርጫ ክልሎች አቤቱታ ያለባቸው ሲሆን በሶማሌ ክልል ሁለት የምርጫ ክልሎች አቤቱታ አለባቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም