አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 556 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

90

አርባ ምንጭ ፣ መስከረም 29 /2014 (ኢዜአ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስኮች ያስለጠናቸውን 6 ሺህ 556 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው እያሰመረቃቸው ከሚገኙት መካከል  6 ሺህ 34 በመጀመሪያ ዲግሪ  ፣517  በሁለተኛ ዲግሪ እና  አምስት  ተማሪዎች ደግሞ በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ  የዛሬውን ሳይጨምር ቀደም ባሉት ዓመታት ከ63 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተመልክቷል።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ዶክተር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና በኢትዮጵያ የኢንዶኔዢያ አምባሳደር አል ቡስይራ ባስኑር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም