ዋልያዎቹ ነገ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ይጫወታሉ

መስከረም 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግርኳስ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛ ጨዋታውን ነገ በባህርዳር ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያደርጋል።

ለኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ኢትዮጵያ ከጋና፣ ዚምባብዌና ደቡብ አፍሪካ ጋር በምድብ ሰባት መደልደሏ ይታወቃል።

በምድብ ድልድሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጋና 1 ለ 0 ሲሸነፍ የዚምባቡዌ አቻውን ደግሞ 1ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል።

ዋልያዎቹ ነገ ምድቡን በአራት ነጥብ ከሚመራው የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ቡድን ጋር በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነገ የሚጋጠሙት የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ባህርዳር መግባታቸው ታውቋል።

በዚሁ ምድብ የሚገኘው የጋና ብሔራዊ ቡድን ነገ በሜዳው የዚምባቡዌ ብሔራዊ ቡድንን ያስተናግዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም