ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች የተለያዩ ሹመቶች ሠጡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች የተለያዩ ሹመቶች ሠጡ
መስከረም 27/2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በዛሬው በከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ላይ ሹመቶችን ሠጥተዋል።
በዛሬው እለት ሹመት የተሰጣቸው ሃላፊዎች አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስትር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-
1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ
5፡- ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤ -
6 :- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ
7:- አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡