ቀጥታ፡

የሶስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮች የካቢኔ አባል ሆኑ

መስከረም 26/2014 (ኢዜአ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲዎች አመራሮች የካቢኔ አባል ሆነው ተመረጡ።
ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 22 የካቢኔ አባላትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለካቢኔ አባላት ሹመት ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል

የኢትዮጵያ ዜጎች ማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር ፣

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጄላ መርዳሳ - የባህልና ስፖረት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀደም ሲል የተፎካካሪ ፓርቲዎች በሃላፊነት እንደሚሾሙ መናገራቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የተለያዩ ተፊካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ የመንግስት ሃላፊነቶች ተሹመዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ22 ካቢኔ አባላትን ሹመት በ2 ተቃውሞ፣ በ12 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

በእለቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቆ መኮንን እንዲሁም ሌሎች የተሾሙ የካቢኔ አባላት በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም