ኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ቁጥጥር የሚያደርግ ጥምር ጦር ለማስፈር ተስማሙ

118
ነሃሴ 11/2010 ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ድንበር ቁጥጥር የሚያደርግ ጥምር ጦር ለማስፈር ከስምምነት ላይ  ደርሰዋል። ኢትጵያና ሱዳን በሚያዋስኗቸው ድንበር  ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ የጋራ ጦር ለማሰማራት የተስማሙት የሁለቱ ሀገራት የጦር ኢታማዦር ሹሞች  በሱዳን  ባካሄዱት ውይይት ነው፡፡ የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ከማል አብዱል መዕሩፍ  እንደገለጹት  የሚቋቋመው  ምር ጦር   ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ ድንበር እየተሻገሩ  በቡድን ጥቃት የሚፈጽሙ አካላትን፣  ህገ-ወጥ ስደትን ና የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል  ነው፡፡ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን በበኩላቸው  የሁለቱ ሀገራትበትብብር  መስራት  የድንበር አካባቢን ሰላምና ደህንነት  ለማስጠበቅ ከፍተኛ ድርሻ አለው ፡፡ “በጋራ የሚቋቋሙት ወታደሮችም  የድንበሩን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ጉልህ ሚና ይጫወሉ”ብለዋል፡፡ ምንጭ፡- አናዱሉ የዜና ወኪል    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም