በበዓለ ሲመቱ የታደሙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ወደ አገራቸው ተመለሱ - ኢዜአ አማርኛ
በበዓለ ሲመቱ የታደሙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ወደ አገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25/2014 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ወደ አገራቸው ተመለሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ሽኝት አድርገውላቸዋል።
የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ፣ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሓመድ ቡሃሪ፣ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፣የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሓመድ አብዱላሂ ሞሓመድና የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራማታን ላማምራ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂን-ሚሼል ሳማ ሉኮንዴ ትላንት ምሽት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ መንግሥት መመሥረት የሚያስችል ድምጽ በማግኘቱ ተከትሎ ትላንት ዶክተር አብይ አህመድ በቀጣይ አምስት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲመሩ መሰየማቸው ይታወቃል።