በኢትዮጵያ የነበረውን የቅራኔ ፖለቲካ ሴራ በማፍረስ በህዝብ ዘንድ አብሮነትን ማጠናከር ዋነኛ ትኩረታችን ይሆናል - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የነበረውን የቅራኔ ፖለቲካ ሴራ በማፍረስ በህዝብ ዘንድ አብሮነትን ማጠናከር ዋነኛ ትኩረታችን ይሆናል
አዲስ አበባ መስከረም 25/2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የነበረውን ፖለቲካ ሴራ በማፍረስ በህዝብ ዘንድ አብሮነትን ማጠናከር ዋነኛ ትኩረታችን ይሆናል ሲሉ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉኤዎች ተናገሩ።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ሕዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ አዲስ የተመሰረተው መንግሥት ኢትዮጵያውያን በችግር ውስጥ አልፈው ብርሃን የሚያዩበት የአዲስ ምዕራፍ ጅማሮ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የነበረውን ፖለቲካ ሴራ በማፍረስ በህዝብ ዘንድ አብሮነትን ማጠናከር ዋነኛ ትኩረታችን ይሆናል
ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን በማጉላት ቀደም ሲል በኢትዮጵያውያን መካከል ቅራኔ እየሰፋ እንዲሄድ የተሰራው ሴራ ተወግዶ ወደ አገራዊ ግንባታና አብሮነት እንዲሸጋገር እንሰራለን ብለዋል።
በክልሎች መካከል ወንድማማችነትት በማጠናከር ሕብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተጠናከረባት ኢትዮጵያን መገንባት የሚያስችሉ የተለያዩ መድረኮችን እንደሚያካሂዱ ጠቁመዋል።
መከፋፈልንና ጥላቻን በማስወገድ ፍቅርና አንድነት ሊያጠናክሩ የሚችሉ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት እናደርጋለንም ነው ያሉት።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ፤ በክልሎች መካከል ያለውን የእርስ በእርስ ግንኙነትና አብሮነት በማጠናከር ዘላቂ ሰላም መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የምንስራበት ምእራፍ ነው ይላሉ።
ኢትዮጵያውያን ነገን ተስፋ በማድረግ ድምጽ የሰጡት መንግሥት ከሌላው ጊዜ የተለየ ኃላፊነት ያለው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ ናቸው።
የሕብ ለሕብ ግንኙነትን በማጠናከር አንድነትን መፍጠር በቀጣይ በክልሉ በትኩረት ከሚሰሩ ተግባራት መካከል መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የመሰረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ ፍትሃዊ የበጀት ቀመር ድልድል፣ የማልማትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችን በቀጣዩ አምስት አመታት ለመመለስ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትህና እኩልነትን ለማረጋገጥና ወንድማማችነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮችና ፌደሬሽን ምክር ቤት የሥራ ዘመን ትናንት በይፋ ተጀምሯል።