የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡኻሪ አሸኛኘት ተደረገላቸው

81

መስከረም 25/ 2014 (ኢዜአ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ የታደሙት የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡኻሪ ዛሬ ወደ አገራቸው አቅንተዋል።

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዝዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

በአሸኛኘት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም