በሀገር ሰላም እንዲመጣና አዲሱ መንግስት የተረጋጋ እንዲሆን የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሀገር ሰላም እንዲመጣና አዲሱ መንግስት የተረጋጋ እንዲሆን የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
መስከረም 25/2014(ኢዜአ) በሀገር ሰላም እንዲመጣና አዲሱ መንግስት የተረጋጋ እንዲሆን በሃይማኖት አባቶች የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው የጸሎት ስነስርዓት የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የሁሉም ቤተእምነት የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
የጸሎት መርሐ ግብሩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሲሆን፤ ለአገር ሰላምና በህዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግስት ተረጋግቶ አገር እንዲመራ በሚል ነው።
ስለ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ እንዲሁም መሪዎቿ ላይ ባተኮረ ፀሎታቸው በኢትዮጵያ መጭው ጊዜ የሰላም የአንድነት፣ የልማትና የብሩህ ተሰፋ እንዲሆን ፀሎት አድርገዋል።