የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ መስከረም 24/2014 የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ዬዌር ሙሴቨኒ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የ77 ዓመቱ ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ከእ.አ.አ 1986 አንስቶ የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ሆነው አገሪቷን እየመሩ ይገኛሉ።የዩጋንዳ ገዢ ፓርቲ ናሽናል ሬዚስታንስ ሙቭመንት ሊቀ-መንበርም ናቸው።
ዩዌሪ ሙሴቬኒ በሕዳር ወር 2013 ዓ.ም በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በነበራቸው ውይይት “ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ ቀደምት አገራት የምትጠቀስና ቅኝ ያልተገዛች አገር ናት፤ኢትዮጵያ የአፍሪካ ክብር ነች” ማለታቸው የሚታወስ ነው።ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምስረታ ጉባኤ ዛሬ ከቀትር በፊት የተካሄደ ሲሆን፤ ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸው ይታወቃል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ-ሲመት በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል።በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ለመታደም ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ አዲስ አበባ ገብተዋል።ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባባል አድርገውላቸዋል።