ቀጥታ፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን በዓለ ሲመት ለመታደም በርካታ ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ በማቅናት ላይ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24/2014 (ኢዜአ) በ6ኛው ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የዶ/ር ዐቢይ አሕመድን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በመሾሙ ፤በዓለ ሲመቱ ላይ ለመታደም እና የመንግስት ምስረታውን ለመደገፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ መስቀል አደባባይ በመጓዝ ላይ ይገኛል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ከሰዓት በኋላ በመስቀል አደባባይ የሚከናወን ሲሆን የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሚከናወን ይሆናል፡፡

መረጃው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተሪያት ፅህፈት ቤት ነው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም