ቀጥታ፡

የአልጀሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በምትመሰርተው አዲስ መንግስት ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ

መስከረም 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራማታን ላማምራ ኢትዮጵያ ዛሬ በይፋ በምትመሰርተው አዲስ መንግስት በክብር እንግድነት ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታው ሬድዋን ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ልዑኮቻቸው ኢትዮጵያ ነገ በይፋ በምትመሰርተው አዲስ መንግስት መርሃ ግብር ላይ ለመታደም አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያም በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የሚያስተዳድራትን መንግስት በይፋ ለመመስረት ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ኢትዮጵያና አልጀሪያ ከ1960 ጀምሮ ጠንካራ አህጉራዊ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት በመፍጠር በትብብር ላይ የተመሰረተ ንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በመስራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም