የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በኢትዮጵያ የመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በኢትዮጵያ የመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ነገ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ።
ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢትዮጵያና ሴኔጋል በፓን አፍሪካዊ መንፈስ ለማጠናከር በአህጉራዊና የሁለትዮሽ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በዳካር ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወቅት መምከራቸው አይዘነጋም።
ሌሎች አገራት መሪዎችም የመንግስት ምስረታ ስነ ስርዓቱን ለመታደም አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።