6ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
6ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሂዳል፡፡
በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ጉባኤ ላይም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደርጋሉ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የአለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመስራች ጉባኤው ላይ እንደሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢዜአ የላከው መረጃ ያሳያል።