የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23/2014(ኢዜአ) የኢፌዲሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ ስለሚመጡ እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች ፣ጠቅላይ ሚኒስትሮች ፣ የሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የክልል ፕሬዚደንቶች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በሚገኙበት መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም የኢፌዲሪ መንግስት ይመሰረታል፡፡
የመንግስት ምስረታው በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም የኢሬቻ እና የመስቀል በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡
የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን እያቀረበ የመንግስት ምስረታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ 7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል 8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል 13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርስቲያን19. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል
20. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል 21. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
22. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
23. ጎርጎሪዮስ አደባባይ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ፡፡
ፕሮግራሙ በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ/ ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫዎች ግራና ቀኝ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት ግብረኃይል አስታውቋል፡፡
እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ ግብረ ኃይሉ መልዕክቱ አስተላልፏል።