ቀጥታ፡

ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ ሆኑ

መስከረም 22/2014 የመንግስት ምስረታ ጉባኤ እያካሄደ ያለው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎን የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል ።
አፌ ጉባኤውን ያቀረቡት የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ናቸው ።

አቶ ጥላሁን 6ኛው ምርጫ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ ይችላል ብለው በህዝብ በመመረጥ ቦታ ብንይዝም አሸናፊው ህዝቡ ነው ብለዋል ።

ቀጣይ በሚኖረው ጊዜ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝባችን ተጠቃሚነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል ።

ወይዜሮ ፋጤ ስርሞሎ ከወረዳ ጀምሮ በክልሉ በተለያዩ የስራ ሀላፊነት በብቃት ማገልገላቸው ተገልጿል ።

ወይዘሮ ፋጤ በክልሉ ብልጽግና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሆነው ሰርተዋል።

ተሿሚዋ የተጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም