አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ
መስከረም 22/2014 (ኢዜአ) አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ ።
አቶ ርስቱ ለበርካታ ዓመታት ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው ውጤታማ አፈጻጸም የነበራቸው መሆኑን ገልጸዋል ።
ስነምግባር ተነሳሽነት ታማኝነትና ትጋት እንዲሁም የአመራር ብቃት እንዲመረጡ ያደረጋቸው መሆኑን ገልጸዋል ።
በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙ ችግሮችን በበሳል አመራር በማሻገር አሁን ላለው ልማት ማድረሳቸውን ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በቀረቡት ዕጩ አስተያየት በመስጠት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ።
አቶ ርስቱ ይርዳው የተጣለባቸውን ሀላፊነት በታማኝነት ለመወጣት በምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል ።