ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚካፈሉበት የለንደን ማራቶን ነገ ይካሄዳል

102

አዲስ አበባ መስከረም 22/2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚካፈሉበት 41ኛው የለንደን ማራቶን ነገ ይካሄዳል።

በወንዶች መካከል በሚካሄደው ውድድር ያለፈው ዓመት የዚሁ ማራቶን አሸናፊ ሹራ ቂጣታ ይካፈላል።

አትሌት ብርሃኑ ለገሰ፣ ሞስነት ገረመው፣ ሲሰይ ለማ፣ ክንዴ አጣነውም በነገው ውድድር ይካፈላሉ።

በሴቶች ውድድርም በቶኪዮ ኦሊምፒክ 4ኛ ደረጃን ያገኘችውን አትሌት ሮዛ ደረጄን ጨምሮ ብርሃኔ ዲባባ፣ ደጊቱ አዝመራው፣ ዘይነባ ይመር እና ትዕግስት ግርማ ተሳታፊዎች ናቸው።

በሴቶቹ ውድድር ባለፈው ዓመት በለንደን ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ኬንያዊት ብሪጅድ ኮስጌና እስራኤላዊቷ ሎና ሳልፒተር ጥሩ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም