በሐረሪ ክልል በምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ተጠናቆ የድምጽ መስጫ ሳጥኖች እየተጓጓዙ ነው

71

መስከረም 21/2014 (ኢዜአ) በሐረሪ ክልል በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደት በመጠናቀቁ የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደ ምርጫ ክልል በመጓጓዝ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጊዜያዊ ውጤቶችም በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፋቸውም ተገልጿል።

የክልሉ ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ቦጋለ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የድምጽ መስጠት ሒደቱ በሰላም ካለቀ በኋላ በየጣቢያዎቹ የተካሄደው የድምፅ ቆጠራ ተጠናቋል።

በዛሬው ዕለትም የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደ ምርጫ ክልል የማጓጓዝ ስራ እየተካሔደ ነው።

መራጩ ሕዝብም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻው ውጤት እስኪ ገለጽ እንዲጠባበቅ ጠይቀዋል።

በትናንትናው ዕለት በክልሉ ሲካሄድ የዋለው ምርጫ በሠላም መጠናቀቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም