ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል የተካሄደው ምርጫ ተጠናቀቀ ፤የድምፅ ቆጠራም ተጀምሯል

ጅግጅጋ፣ መስከረም 20/2014( ኢዜአ ) በሶማሌ ክልል ዛሬ የተካሄደው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ፤ የድምፅ ቆጠራም ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ነፃነት በቀለ እንዳስታወቁት  በክልሉ በተቋቋሙ 3ሺ978 ምርጫ ጣቢያዎች ህዝቡ ያለምንም ችግር በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈልጋቸውን ዕጩዎች መርጧል።


በአሁኑ ሰዓትም ምርጫው የሕዝብና የተመራጮች እንዲሁም አገር አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎችና የሲቪክ ማህበራት በተገኙበት የድምፅ ቆጠራ መጀመሩን ገልጸዋል።

በክልሉ ለተካሄደው ምርጫ ከአምስት ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውንም አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም