ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2014(ኢዜአ) ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጐችን መልሶ ለማቋቋም የሁሉም ሀይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ሊካሔድ ነው።
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መርሀ ግብሩን አስመልክቶ ሁሉም ሃይማኖቶች በጋራ ሰለሚያከናውኑት ተግባራት መግለጫ እየሰጠ ነው።
መርሃ ግብሩን የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በበላይነት እንደሚመራው ተጠቁሟል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ በዋናነት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል ነው።
ከየሀይማኖት ተቋማቱና ምእመናን የሚሰበሰበው ገንዘብ አንድ ቋት እንዲኖረው ለማስቻል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት መከፈቱም ተጠቁሟል።
የሰብዓዊ ድጋፉን በሚመለከት ከጉባኤው እና ከሰላም ሚኒስቴር የተወጣጡ አባላት ያሉት አቢይ ኮሚቴ መዋቀሩም ተነግሯል።
ምዕመናን በቤተ እምነቶቻቸው አማካኝነት የሚቀርብላቸውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል ምላሽ እንዲሠጡ መልእክት ተላልፏል።