ቀጥታ፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳደር የቀረቡ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ

ባህርዳር መስከረም 20/2014 (ኢዜአ) አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ያቀረቧቸው 27 የቢሮ ኃላፊዎች ሹመትን ምክር ቤቱ ተቀብሎ አፀደቀ።

ተሿሚዎቹ ወቅታዊ የትምህርት ዝግጅታቸውንና የስራ ብቃታቸውን ታሳቢ አድርገው የተሾሙ መሆናቸውንም ዶክተር ይልቃል አብራርተዋል

ተሿሚዎቹ ክልሉን አሁን ካለበት ውስብስብ ችግር በማውጣት ህዝቡን ወደላቀ ልማትና የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር ያስችላሉ ተብሎም ዕምነት እንደተጣለባቸው ገልጸዋል።

ከአጠቃላይ ተሿሚዎች መካከልም 75 በመቶ አዲስ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ከነባር አመራሮች የተሾሙ መሆናቸውን አስረድተዋል

ከአጠቃላይ ተሿሚዎች መካከልም አቶ ጣሂር መሃመድ ከአብን እና አቶ ተስፋሁን አለምነህ ከአዴሃን ፓርቲዎች እንዲካተቱ መደረጉንም አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት፤ 

1.እጩ ዶክተር ጌታቸው ጀምበር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር

2.ዶክተር ሰማ ጥሩነህ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ

3.ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ

4.አቶ ስዩም መኮነን በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።

5.ዶክተር ጥሁን መሃሪ የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ

6.አቶ አረጋ ከበደ የስራ ፈጠራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

7.አቶ ገረመው ገብረፃድቅ ለፍትህ ቢሮ ኃላፊ

8.ወይዘሮ አስናቁ ድረስ ለሴቶችህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

9.አቶ ግዛቸው ጥሩነህ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

10.ዶክተር ማማሩ አያሌው የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

11.የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ 

12.አቶ ኃይሌ አበበ የማዕድን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሌ አበበ

13.ዶክተር ማተቤ ታፈረ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

14.ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው ለግብርና ቢሮ ኃላፊ

15.ሜጀር ጄኔራል መሰለ በለጠ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ

16.አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ

17.ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም የስቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

18.አቶ መሃመድ ያሲን የክልሉ መንገድ ቢሮ ሃላፊ

19.አቶ አማኑኤል ፈረደ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

20.ዶክተር ፀጋ ጥበቡ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 

21.አቶ ሲሳይ ዳምጤ የመሬት ቢሮ ኃላፊ 

22.አቶ ጣሂር መሃመድ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ከተፎካካሪ ፓርቲ አብን

23.አቶ ተስፋሁን አለምነህ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ ከአዲሃን ።

24.አቶ የአንሙት በለጠ የፕላን ልማት ቢሮ ሃላፊ 

25.አቶ ቢያዝን እንኳሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ 

26.አቶ እንድሪስ አብዱ የኢንዲስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ

27.ዶክተር ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ኢንዲሾሙ ለምክር ቤቱ የቀረቡ ተሿሚዎች ሹመትን አፅድቋል።

ተሿዎቹም መንግስትና ህዝብ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም