ምርጫ በሚካሄድባቸው ሐረሪና ሶማሌ ክልሎች ስራ ዝግ ይሆናል - ኢዜአ አማርኛ
ምርጫ በሚካሄድባቸው ሐረሪና ሶማሌ ክልሎች ስራ ዝግ ይሆናል
መስከረም 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሐረሪና ሶማሌ ክልሎች በምርጫው ምክንያት ስራ ዝግ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።
የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሶሊያና ሽመልስ፤ ምርጫውን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም 6ኛው አገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ነገ ድምጽ እንደሚሰጥ አስታውሰዋል።
"በመሆኑም ምርጫው ነገ ድምፅ በሚሰጥባቸው አካባቢዎች ስራ ዝግ ይሆናል" ብለዋል።
በዚህም በሀረሪና ሶማሌ ክልሎች ሙሉ በሙሉ እንዲሁም በደቡብ ክልል ነገ ድምጽ በሚሰጥባቸው አካባቢዎች እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ስራ ዝግ እንደሚሆን ጠቁመዋል።