ቀጥታ፡

የአገር ግንባታ ስራዎች ከዛሬ በተጨማሪ የነገ የኢትዮጵያ አቅሞችን የሚመለከቱ መሆን አለባቸው

አዲስ አበባ መስከረም 19/2014 (ኢዜአ) የአገር ግንባታ ስራዎች ከዛሬ በተጨማሪ የነገ የኢትዮጵያ አቅሞችን የሚመለከቱ መሆን አለባቸው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክረተሪያት አሰናጅነት የሚካሄደው አዲስ ወግ የውይይት መድረክ “በአዲስ መንፈስ አዲስ ውል- የመንግስት ምስረታ እና አገር ግንባታ” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል።

አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሚያካሂዳቸው የአገረ መንግስት ግንባታ ስራዎች ላይ ውይይቱ ያተኮረ መሆኑም ተገልፇል።

በመድረኩ ላይ የአገር ደህንነት፣ ምጣኔ ሃብት ጉዳዮች እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ ስራዎችን በተመለከተ በተለያዩ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቧል።

በመድረኩ ላይ ከፅሁፍ አቅራቢዎቹ፤ የአገር ግንባታ ስራዎች ከዛሬ በተጨማሪ የነገ የኢትዮጵያ አቅሞችን የሚመለከቱ መሆን እንዳለባቸው ተነስቷል።

የመወያያ ነጥቦቹን መነሻ በማድረግ የመድረኩ ታዳሚዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ከማንሳት በተጨማሪ ተጨማሪ ሃሳቦችና አስተያየቶችን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም