መስቀል ከኢትዮጵያም ባለፈ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ በመሆኑ ጠብቀን ለትውልዱ ማስተላለፍ አለብን - ኢዜአ አማርኛ
መስቀል ከኢትዮጵያም ባለፈ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ በመሆኑ ጠብቀን ለትውልዱ ማስተላለፍ አለብን
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17/2013 (ኢዜአ) መስቀል ከኢትዮጵያም ባለፈ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ በመሆኑ ጠብቀን ለትውልዱ ማስተላለፍ አለብን።
የመስቀል ደመራ በአል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሰት የስራ ሃላፊዎች የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
ከእለቱ ታዳሚዎች መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው አሸናፊ ላቀውና ወይዘሮ የሺህወርቅ ወንዴ ፤ መስቀል ከኢትዮጵያም ባለፈ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ በመሆኑ ጠብቀን ለትውልዱ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።
የመስቀል በዓል አከባበር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ 2005 ዓ.ም ተመዝግቧል።
በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፍቅርና አብሮነት ተምሳሌት ሆኖ የሚከበር ሲሆን የኢትዮጵያን ደግሞ የጋራ ሃብታቸው ሆኗል።
በዓሉ ከኢትዮጵያም ባለፈ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ በመሆኑ በጋራ ጠብቀን ለትውልድ ልናስተላልፈው ይገባል ብለዋል።
የትኛውም ጉዳይ ያለ ሰላም የሚከወን ባለመሆኑ ለኢትዮጵያ ሰላምና ህልውና ቅድሚያ መስጠት አለብንም ነው ያሉት።
የመስቀል በዓል፣ የጥምቀት በዓል፣ ከገዳ ሥርዓት የኢሬቻ በዓል እና ፍቼ ጨምበላላ በኢትዮጵያ የማይዳሰሱ ቅርሶች ሆነው በዓለም ቅርስነት መመዝገባቸው ይታወቃል።