ቀጥታ፡

"የኢትዮጵያ ምንጊዜም እውነትን ይዛ የምትራመድ አገር በመሆኗ የተሸነፈችበት የታሪክ አጋጣሚ የለም"

መስከረም 13 / 2014 (ኢዜአ)  "የኢትዮጵያ ምንጊዜም እውነትን ይዛ የምትራመድ አገር በመሆኗ የተሸነፈችበት የታሪክ አጋጣሚ የለም፤ ወደ ፊትም አይኖርም" ሲሉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናገሩ።
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሠራተኞች "የነጩን ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግሥት" ንቅናቄ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ አየለች እሸቴ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት "የኢትዮጵያ ምንጊዜም እውነትን ይዛ የምትራመድ አገር በመሆኗ የተሸነፈችበት የታሪክ አጋጣሚ የለም፤ ወደ ፊትም አይኖርም" 

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነታ ለዓለም በምታስረዳበት ኩነት ላይ በመሳተፋችን ተደስተናል ብለዋል።

በውጭም ሆነ በውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ለአገራቸው ክብርና ህልውና ሲሉ እያደረጉት ያለው አብሮነት የሚያኮራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

"የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት" ንቅናቄ ከመስከረም 3 እሰ 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።

በንቅናቄው በአገር አቀፍ ደረጃ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዘመቻው ዋነኛ አላማ አንዳንድ የዓለም አገሮች በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን ያልተገባ ጫና በመቃወም እውነታውን ለአለም አቀፉ ማሳየት ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም