የኢትዮጵያ ህዝብ በአገሩ ክብርና ሉአላዊነት አይደራደርም - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ህዝብ በአገሩ ክብርና ሉአላዊነት አይደራደርም
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህዝብ በአገሩ ክብርና ሉአላዊነት አይደራደርም።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" መርሃ ግብርን አከናውነዋል።
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለብርሃን ዜና፤ ባስተላለፉት መልእክት አሸባሪው ህወሃት በእብሪት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የአሸባሪው ድርጊትም በአገሩ ለማይደራደረው የኢትዮጵያ ህዝብ እልህና ቁጣ ማስከተሉን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የሚሹ አገራትም የአሸባሪውን ግልፅ ድርጊት አይተው እንዳላዩ በማለፍ ይባስ ብሎ በመንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።
እነዚህ አገራት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የህልውና ዘመቻ እውነታውን ለመገንዘብ ፍላጎት እንደሌላቸው በተለያየ መንገድ አሳይተዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ለአገሩ ክብርና ሉአላዊነት በጋራ መቆሙን አድንቀው የዚሁ ማሳያ በሆነው "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ዘመቻ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ይህንኑ ዘመቻ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
ዘመቻው ከአሸባሪው ኃይል ጋር በጭፍን እየተባበሩ ላሉ አካላት ግልፅ መልእክት ያስተላልፋል ብለዋል።