አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅትን የቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅትን የቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ
መስከረም 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅትን የቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ።
የሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ግምቱ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድርጅት በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ያደረገውን የቁሳቁስ ድጋፍ የድርጅቱ የክብር አምባሳደር አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በተገኘበት ለደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ አስረክቧል።
ድጋፉ በዋናነት የምግብ ፍጆታዎች፣ አልባሳት፣ የንጽሕና መጠበቂያ፣ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ግብዓቶችና ሌሎችንም ያካተተ ነው።