ቀጥታ፡

የሽብር ቡድኑ በአማራ ክልል በርካታ ሕዝብ ለከፋ መጎሳቆል እንዲዳረግ አድርጓል

መስከረም 13/2014(ኢዜአ) የህወሓት ተሽብር ቡድን በአማራ ክልል በርካታ ሕዝብ ለከፋ መጎሳቆል እንዲዳረግ ማድረጉ ተገለጸ።

የላልይበላ የባህል ቡድን በወሎ ግንባር ተሰልፎ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እየተፋለመ ለሚገኘው ሚሊሻ የተሃድሶ እና የማነቃቂያ ዝግጅት አቅርቧል።

በማነቃቂያ መርሃግብሩ ላይ የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ መኮንን የአሸባሪውን የህወሓት ኃይል እኩይ ዓላማን ለማክሸፍ ታሪክ የማይረሳው አኩሪ ተጋድሎና ጀብዱ እየተፈጸመ ነው ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ በአማራ ክልል በርካታ ሕዝብ ለከፋ መጎሳቆል እንዲዳረግ ማድረጉንም ነው የገለጹት።

በወራሪው ሃይል በሕዝብ ላይ እየደረሰ ካለው መከራና ስቃይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል በጽናት ታግሎ ሽብርተኛውን ቡድን ማጥፋት ይገባልም ብለዋል።በወሎ ግንባር የሚገኙ የሚሊሻ አባላት አኩሪ ድል እንደሚያስመዘግቡ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም