ኢዜማ በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ኢዜማ በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ መስከረም 13/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀያቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን የኢዜማ አመራርና አባላት በደሴ ትግል ፍሬ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተጠለሉ ዜጎች እንዲውል አስረክበዋል።
የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ዳዊት ብርሃኑ ድጋፉን ለወገን ደራሹ ወገን ነው በሚል ከፓርቲው አባላት፣ አመራሮችና ሠብዓዊነት ከሚሰማቸው ዜጎች በማሰባሰብ ማምጣታቸውን ገልጸዋል።
የኢዜማ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ቅድስት ግርማይ በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መደገፍ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።