ቀጥታ፡

በምርጫው የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ

ሐረር፤ መስከረም 12/ 2014(ኢዜአ) መስከረም 20/2014ዓ.ም.በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀናል ያሉትን ዕጩ ተወዳዳሪ ከወዲሁ ለይተው ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት  አመልክተዋል፡፡

ከነዋሪዎቹ መካከል  አቶ አብራሂም ኡስማን  የምርጫ ካርድ ወስጃለው፤የድምጽ መስጫ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነኝ ነው ያሉት።

በተለይ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ፣ተአማኒ እና ፍትሃዊ  በሚደረገው እንቅስቃሴ በመሳተፍ  ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የሀገሪቱን ብሎም የክልሉን እድገት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ይበጃል ያሉትን ዕጩ ተወዳዳሪ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል አቶ አብራሂም።

ወይዘሮ ዊዳት እንድሪስ፤መብታቸውን ተጠቅመው ያመኑበትን የፓርቲ ዕጨ ተወዳዳሪ ከወዲሁ ለይተው ለመመረጥ መሰናዳታቸውን ገልጸዋል።

ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።

ወጣት ዚያድ ሙስ፤ጠፋ በበኩሉ፤ መስከረም 20/2014ዓ.ም. በሚካሄደው  ጠቅላላ ምርጫ በመሳተፍ ለሀገርና ክልሉ ሰላምና ልማት ይበጃል ያለውን ዕጩ  ለመምረጥ  መዘጋጀቱን ተናግሯል።

ህዝቡም በዕለቱ ለሀገር የሚበጀውን ፓርቲ በመመረጥ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እንዲጎለብት ሚናው ማጎልበት እንዳለበት አመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተለያዩ ፓርቲዎች አበረታች እንቅስቃሴዎችን እያከናወኑ ስለመሆኑም  ወጣት ዚያድው አንስቷል፡፡

ከሁሉም የሀገር ሰላም ይበልጣል፣ በተለይም ወጣቶች ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሚናችንን መወጣት አለብን ብሏል።

በምርጫው በመሳተፍም መበትና ጥቅማቸውን ያስከብርልኛል ብለው ያመኑበትን ለመመረጥ መዘጋጀታቸውን አቶ አሰፋ ዋሴ አስታውቀዋል፡፡

መምህርት ትዕግስት ተገኔ በበኩላቸው፤ የሚበጀኝን ለመምረጥ የድምጽ መስጫ ቀንን በጉጉት እየጠበቅኩ ነው  ብለዋል።

ህዝቡ የወሰደውን ካርድ በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት መምህርት ትዕግስት ፤ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከማድረግ አንፃርም ህዝቡ በተለይም ወጣቱ እያከናወነ የሚገኘውን አበረታች ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም