ም/ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ም/ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
መስከረም 12/2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓኮሜ ሞቤሌት ቡቤያ ጋር በኒውዮርክ ተወያይተዋል።
በውይይቱ የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ተነስተዋል።በቅርቡ ጋቦን በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቀጣይ አባል መሆኗን ተከትሎ፤ ለአፍሪካውያን ድምፅ በመሆን ሚናዋን እንደምትወጣ ያላቸውን ዕምነት አቶ ደመቀ ገልፀዋል።
የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ቀንድ ያለው ትኩረት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ፤ አፍሪካዊ ችግሮችን አፍሪካውያን መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት