የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የዲፕሎማቶች ቀዳሚ ስራ መሆን አለበት

128

መስከረም 11/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የዲፕሎማቶች ቀዳሚ ስራ መሆን አለበት ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

ከኢፌዴሪ ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች አስመልክቶ ከመስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛል።

ስድስተኛ ቀኑን በያዘው ስልጠና ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዲፕሎማሲው መስክ ያላቸውን ልምድ አጋርተዋል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በመስኩ የአገራቸውን ጥቅም ማስጠበቅና በስራቸው ከምንም በላይ አገርን መውደድና ማስቀደም አለባቸው ብለዋል።

May be an image of one or more people and indoor

"ዲፕሎማቶች የአላማ አንድነት ሊኖራቸው ይገባል ፤ከባድ ሁኔታዎችን መሸከም አለባቸው፤ የማያወላውል አቋምና የአገር ፍቅር ሊኖራቸው ይገባል" ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ አስታውቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የፖለቲካ መሳሪያ ሳይሆን "ልክ እንደ ወታደር" ከምንም ስርዓት ተሻግሮ መሄድ አለበት ብለዋል።

"አገር ከሌለ የሚያከብረን ማንም የለም" ያሉት ፕሬዝዳንቷ ታላቋን ኢትዮጵያ ተረባርቦ መገንባት እንደሚገባ አመልክተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሚሲዮኖች፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች በተዘጋጀው ስልጠና መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ሚኒስቴሩ ሲያካሄድ የቆየው መዋቅራዊ ለውጥ እና የአደረጃጀት ክለሳ ተጠናቆ ጥቅምት ወር መጨረሻ ተግባራዊ እንደሚሆን መግለፃቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም