የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሠራተኞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት" ንቅናቄን ተቀላቀሉ - ኢዜአ አማርኛ
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሠራተኞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት" ንቅናቄን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ መስከረም 10/2014 (ኢዜአ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ንቅናቄን ተቀላቅለዋል።
ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፊርማቸውን በማኖር የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም ለማሳወቅ የተጀመረውን ዘመቻ ተቀላቅለዋል።
የተቋሙ ሠራተኞች በምጣኔ ሀብት የተከፈተውን ጦርነት ለመመከት እያከናወኑት ካለው ተግባር ጎንለጎን እውነታውን ለዓለም ለማወቅ ንቅናቄውን መቀላቀላቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በቀጣይም የምጣኔ ሀብት አሻጥሮችን ለመመልከት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታና አሸባሪው የህወሓት ቡድን እያደረሰ ያለውን የሽብር ተግባር ለዓለም ለማሳወቅ እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ ወጣቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ሚኒስትሮችና ፖለቲከኞችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ንቅናቄው እስከ መስከረም 15 የሚቆይ ሲሆን ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ፊርማቸውን በማኖር መልዕክታቸውን ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ይልካሉ።