ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከተሞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ዘመቻን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ከተሞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል።

የከተማ ልማትና ኮስትራክሽን ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸሙና በ2014 በጀት ዓመት ዕቅዱ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

ከውይይቱ ጎን ለጎንም የኢትዮጵያ ከተሞች "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት" ዘመቻን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አስጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሎች የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተል።

መስከረም 3 ቀን 2014 የተጀመረው "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት" ዘመቻ እስከ መስከረም 15 ቀን የሚቆይ ነው።

ዘመቻው የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ለማሳወቅና የአሸባሪውን ህወሓት እኩይ ሴራ ለማጋለጥ ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም