የቱርክ ቀዳማዊት እመቤት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በተመለከተ አዲስ መፅሃፍ ያስተዋውቃሉ

መስከረም 10/2014 (ኢዜአ) የቱርክ ቀዳማዊት እመቤት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን የተመለከተ አዲስ መፅሃፍ በኒውዮርክ የቱርክ ኢምባሲ ሊያስተዋውቁ መሆኑ ተነገረ።የቀዳማዊት እመቤት ኤምኒ ኤርዶጋን መፅሃፍ አፍሪካን ሲጎበኙ የፈጠረባቸውን ስሜትና ትዝታዎችን ያካተተ ነው።

መፅሃፉን ለእናታቸው መታሰቢያ ያደረጉት ቀዳማዊት እመቤቷ እኤአ ከ2014 እስከ 2020 ስለጎበኟቸው 23 ሃገራት ያወሳል፤ ከእነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ፣ አልጄሪያ፣ ሶማሊያ፣ታንዛኒያ፣ሞዛምቢክ እና ሴኔጋል ይገኙበታል፡፡

“ማይ አፍሪካ ትራቭልስ” የተሰኘውን መፅሃፋቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሃገራት መሪዎች ቀዳማዊት እመቤቶች፣ ለተባበሩት መንግስታት እና አለምአቀፍ ተወካዮች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ለውጪ ሃገራት አምባሳደሮች ያስተዋውቃሉ ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ጥቅምት መጀመሪያ በቱርክ ለገበያ ይውላል የተባለው መፅሃፍ በቀጣይ በእንግሊዝኛ፣ፈረንሳይኛ፣ አረቢኛ እና በስዋህሊኛ በአለምአቀፍ አታሚዎች እንደሚታተም መረጃው አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም